የሀገር ውስጥ ዜና

1 ሺህ 174 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

By Mikias Ayele

June 03, 2024

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሳዑዲ ዓረቢያ በችግር ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 174 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ፡፡

የዛሬ ተመላሾች ሁሉም ወንዶች ሲሆኑ ÷ ከእነዚህ ውስጥም  ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ 17 ታዳጊ ህጻናት እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡

ለተመላሽ ዜጎች ተገቢውን ድጋፍና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ሥራ እየተከናወነ እንደሚገኝም የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡