የሀገር ውስጥ ዜና

200 ኢትዮጵያውያን ከኦማን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

By ዮሐንስ ደርበው

June 04, 2024

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦማን ማቆያ ጣቢያዎች የነበሩ 200 ኢትዮጵያውን ወደ ሀገር ቤት መመለሳቸውን የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ለተመላሽ ዜጎች ድጋፍ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ስራ እየተሰራ መሆኑን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡

ከሚያዝያ 29 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ 1 ሺህ 579 ኢትዮጵያውያን ከኦማን ወደ ሀገራቸው መመለሳቸው ተገልጿል፡፡