የሀገር ውስጥ ዜና

የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል

By Meseret Awoke

June 04, 2024

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከነገ ጀምሮ የሁሉም የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት እንዲቀጥል መወሰኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ።

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ታኅሣስ 20 ቀን 2014 ዓ.ም ባደረገው 3ኛ መደበኛ ስብሰባ ባስተላለፈው የነዳጅ ውጤቶች የዋጋ ግንባታ የአፈጻጸም ውሳኔ መሠረት የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በየጊዜው እየተከለሰ ሥራ ላይ እንዲውል ሲደረግ መቆየቱ ይታወሳል፡፡

በዚህም መሰረት ከግንቦት 28 ቀን 2016ዓ.ም ማለትም ከነገ ጀምሮ የሁሉም የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በስራ ላይ በነበረበት ዋጋ እንዲቀጥል መወሰኑን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡