አዲስ አበባ፣ ግንቦት 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፋር ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አወል አርባ የ2016/17 ዓ.ም ክልል አቀፍ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎትን አስጀመሩ፡፡
የበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ የአቅመ ደካሞችን ቤት በማደስ የተጀመረ ሲሆን÷ በክልሉ በሁሉም ከተሞች በተቀናጀ መልክ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተገልጿል፡፡
የበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ በሕዝቡ ዘንድ መረዳዳትና መተጋገዝ ይበልጥ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ያስችላል መባሉን የክልሉ መገናኛ ብዙኃን ዘግቧል፡፡
በተጨማሪም የዜጎችን የኑሮ ደረጃ በማሻሻል ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ችግሮችን ለማቃለል ከፍተኛ ሚና እንዳለውም ነው የተመላከተው፡፡