የሀገር ውስጥ ዜና

በመዲናዋ በተካሄደው የምክክር ምዕራፍ የተሳተፉ አካላት እነማን ናቸው?

By ዮሐንስ ደርበው

June 05, 2024

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአዲስ አበባ ከተማ ባካሄደው የአጀንዳ ልየታ ምክክር ምዕራፍ ላይ ሕብርተሰብ ተወካዮች፣ ተቋማት፣ ማኅበራት፣ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች፣ የመንግሥት አካላት ተወካዮች እና ሌሎች ተሳትፈዋል፡፡

እነዚህ ባለድርሻ አካላት በቡድን የተወያዩባቸውን አጀንዳዎች ግንቦት 26 ቀን 2016 ዓ.ም ለተወካዮቻቸው ሰጥተዋል፡፡

በሂደቱ ሁሉም ተወካዮች በሞደሬተሮች አጋዥነት አጀንዳዎችን አደራጅተዋል፡፡

ግንቦት 27 ቀን 2016 ዓ.ም የአምስቱ ባለድርሻ አካላት ተወካዮች አጀንዳቸውን ለኮሚሽኑ አቅርበዋል፡፡

ኢትዮጵያ እየመከረች ነው!