የሀገር ውስጥ ዜና

1 ሺህ 188 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

By ዮሐንስ ደርበው

June 05, 2024

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሳዑዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 188 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ።

ዛሬ ከተመለሱት ውስጥ 16 ጨቅላ ህፃናትና 20 ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊ ህጻናት እንደሚገኙበት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመልክቷል።

ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ስራ እየተሰራ መሆኑ ተገልጿል።

ከሚያዚያ 04 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እየተደረገ ባለው ጥረት እስካሁን ከ37 ሺህ 500 በላይ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው መመለስ ተችሏል።