አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሣይንስና ፈጠራ ሥራዎች ዐውደ-ርዕይና ውድድር በሆሳዕና ከተማ መካሄድ ጀምሯል፡፡
ዐውደ-ርዕዩ የክልሉ ርዕሰ መሥተዳድር እንዳሻው ጣሰው በተገኙበት “ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልልን የሣይንስ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ማዕከል እናድርግ” በሚል መሪ ሐሳብ ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡
ለሁለት ቀናት በሚቆየው ዐውደ-ርዕይ ላይ መምህራን፣ ተማሪዎች እና ኢንተርፕራይዞችን ጨምሮ ከ100 በላይ የፈጠራ ባለሙያዎች እየተሳተፉ ነው፡፡
በፈቲያ አብደላ