የሀገር ውስጥ ዜና

የሸበሌ፣ ገናሌ ዳዋና የኦሞ ጊቤ ተፋሰሶች አዋሳኝ ክልሎች ፎረም ምስረታ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው

By ዮሐንስ ደርበው

June 06, 2024

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የዋቢ ሸበሌ፣ የገናሌ ዳዋ እና የኦሞ ጊቤ ተፋሰሶች እቅድ የማፅደቅና የተፋሰስ ተጋሪ ክልሎች ፎረም ምስረታ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው።

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዴኤታ አብረሃ አዱኛ (ዶ/ር)፥ ፎረሙ የተቀናጀ የውሃ ሃብት አስተዳደር ስርዓትን ለማስፈን የሚረዳ መሆኑን ተናግረዋል።

የተቀናጀ የውሃ ሀብት አስተዳደርን በማስፈን ተፋሰሶችን ከጉዳትና ብክለት በመጠበቅ ለላቀ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ለማዋል እንደሚያስችልም አንስተዋል።

በመድረኩ የፓርላማ ቋሚ ኮሚቴ አባላት፣ የፌደራል ተቋማት ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎችና የክልል የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

የተፋሰስ እቅዱ የተለያዩ ጥናቶችን በማካሄድ የተዘጋጀ ሲሆን፥ በግምገማ የተለያዩ ግብዓቶች ተካትተውበት ይፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

በአሸናፊ ሽብሩና መላኩ ገድፍ