የሀገር ውስጥ ዜና

አቶ ጥላሁን ከበደ በድሬዳዋ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን እየጎበኙ ነው

By Melaku Gedif

June 08, 2024

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር በድሬዳዋ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን እየጎበኙ ነው፡፡

በጉብኝታቸውም÷በከተማዋ እየተሰራ የሚገኘውን የድሬዳዋ አነስተኛ ግድብ እና የከተማዋን ዘመናዊ ቄራ ግንባታ ሒደት ተመልክተዋል፡፡

በተጨማሪም የድሬዳዋ ከተማ ስቴዲየምና የከተማውን የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ግንባታ ያለበትን ሁኔታ መጎብኘታቸውን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡