የሀገር ውስጥ ዜና

አቶ አሕመድ ሽዴ ከጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) የተላከን መልዕክት ለኳታሩ አሚር አደረሱ

By Melaku Gedif

June 10, 2024

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተላከን መልዕክት ለኳታሩ አሚር ሼክ ታሚም ቢን ሃማድ አል ታኒ አድርሰዋል፡፡

አቶ አሕመድ ሽዴ ከኳታር አሚር ሼክ ታሚም ቢን ሃማድ አል ታኒ ጋር በዛሬው ዕለት ተወያይተዋል፡፡

በውይይቱ ወቅትም አቶ አሕመድ ሽዴ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተላከን መልዕክት ለኳታሩ አሚር ሼክ ታሚም ቢን ሃማድ አል ታኒ ጋር አስረክበዋል፡፡

መልዕክቱ የኢትዮጵያ እና ኳታርን የሁለትዮሽ ግንኙነት እንዲሁም ሀገራቱ በቀጣይ ትብብራቸውን ማሻሻል የሚችሉባቸውን መንገዶች የሚያትት መሆኑ ተመላክቷል፡፡