አዲስ አበባ፣ ሰኔ 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአውሮፓ ዋንጫ ዛሬ ጣልያን እና ክሮሺያ ጥሎ ማለፉን ለመቀላቀል የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡
በ17ኛው የአውሮፓ ዋንጫ ጨዋታ በዛሬው ዕለት ምሽት 4 ሰዓት ላይ የምድብ ሁለት የመጨረሻ ጨዋታዎች ይደረጋሉ።
በዚህ መሰረትም ምሽት 4 ሰዓት ላይ ጣልያን እና ክሮሺያ ጥሎ ማለፉን ለመቀላቀል የሚያደርት ብርቱ ፉክክር ተጠባቂ ነው፡፡
ጣልያን በሁለቱ የምድብ ጨዋታዎች 3 ነጥብ በመያዝ 2ኛ ደረጃን ስትይዝ÷ ክሮሺያ ደግሞ 1 ነጥብ በመያዝ የምድቡ ግርጌ ላይ ተቀምጣለች፡፡
በተመሳሳይ ምሽት 4 ሰዓት ላይ አስቀድማ ወደ ጥሎ ማለፉ የተቀላቀለችው ስፔን በምድቡ ቀዳሚ ሆና ለማጠናቀቅ ከአልባኒያ ጋር የምትጫዎት ይሆናል።