አዲስ አበባ፣ ሰኔ 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ የውጭ ቀጥታ የኢንቨስትመንት የስበት ማዕከል መሆኗን የተባበሩት መንግስታት የንግድ እና የልማት ኮንፈረንስ ሪፖርት አመላከተ፡፡
ድርጅቱ ባለፈው ሳምንት ባወጣው ሪፖርት ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ ጠንካራ የኢኮኖሚ እድገት በማስመዝገብ ረገድ ቀዳሚ መሆኗን አመላክቷል፡፡
እንደ ሪፖርቱ ገለጻ ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ 2023 3 ነጥብ 3 ቢሊየን ዶላር የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት በመሳብ ከጎረቤቶቿ ኬንያና ኡጋንዳ ቀዳሚ ነች፡፡
ባለፉት 10 ወራትም 3 ቢሊየን ዶላር የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት መሳቧን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽነር ሃና አርአያስላሴን ጠቅሶ ሪፖርቱ ይፋ አድርጓል፡፡