የሀገር ውስጥ ዜና

አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ በጅቡቲ የተለያዩ ወደቦችን ጎበኙ

By Shambel Mihret

June 25, 2024

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ በጅቡቲ ግንባታው በመጠናቀቅ ላይ የሚገኘውን የዳመርጆግ ወደብን እና የጅቡቲ ዓለም አቀፍ ነጻ የንግድ ቀጣናን ጎበኙ፡፡

በተጨማሪም የኢትዮጵያ አጠቃላይ የገቢ እና ወጪ የምርት ዝውውር የሚካሄድበትን የዶራሌ ሁለገብ ወደብን እና የዶራሌ ኮንቴነር ተርሚናልን መጎብኘታቸውን በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ አመላክቷል፡፡