አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የዘንድሮው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሠራዊቱ በሚገኝበት ሁሉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ አስታወቁ፡፡
ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ በመከላከያ የሎጂስቲክ ዋና መምሪያ ሥር በመልካ-ቃሊቲ አካባቢ በሚገኘው ማዕከል ችግኝ መትከላቸውን እና በሠራዊቱ ደረጃ መርሐ-ግብሩን ማስጀመራቸውን የመከላከያ ሠራዊት መረጃ አመላክቷል፡፡
በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግርም÷ “የምትተክል ሀገር፤ የሚያፀና ትውልድ” በሚል መሪ ሐሳብ በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረው የዘንድሮው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር በሀገር ውስጥም ሆነ በውጪ ሠራዊቱ በሚገኝበት ሁሉ በተጠናከረ ሁኔታ እንደሚከናወን አስታውቀዋል፡፡