አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴሬሽን ምክር ቤት ሰኔ 24 እና 25 ቀን 2016 ዓ.ም 6ኛ የፓርላማ ዘመን 3ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ፣ 2ኛ መደበኛ ጉባኤውን እንደሚያካሂድ ተገለፀ፡፡
ሰኔ 22 ቀን 2016 ዓ.ም ደግሞ ለሁሉም የምክር ቤቱ አባላት የፊሲካል ፌዴራሊዝም መሰረታዊ ጉዳዮችና የኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ በሚል ርዕስ ስልጠና እንደሚሰጥ ተገልጿል፡፡
ምክር ቤቱ መደበኛ ጉባኤውን ከማካሄዱ አስቀድሞ የምክር ቤቱ አራት ቋሚ ኮሚቴዎች ሰኔ 23 ቀን 2016 ዓ.ም ከጉባኤው አጀንዳዎች ጋር ተያያዥነት ባላቸው ርዕሳነ ጉዳዮች ላይ መክረው ለምክር ቤቱ የውሳኔ ሀሳቦች ይዘው እንደሚቀርቡም ታውቋል፡፡
በተጨማሪም ምክር ቤቱ በመደበኛው ጉባኤ ላይ የተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ይሰጣል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተመላክቷል፡፡