የሀገር ውስጥ ዜና

የሱዳን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ሌተናል ጀኔራል መሐመድ ሃምዳን አዲስ አበባ ገቡ

By Tibebu Kebede

June 17, 2020

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 10 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የሱዳን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ሌተናል ጀኔራል መሐመድ ሃምዳን ደጋሎ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ለመምከር አዲስ አበባ ገብተዋል።

ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንቱ አዲስ አበባ ሲገቡ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸውና በጀኔራል አደም መሐመድ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

ሌተናል ጀኔራል መሐመድ ሃምዳን ደጋሎ በቆይታቸው ከሀገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር በሁለቱ ሀገራት ግንኙነትና በወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ እንደሚመክሩ ኢቢሲ ዘግቧል።