የሀገር ውስጥ ዜና

ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) ከኬንያ መንገድ እና ትራንስፖርት ካቢኔ ፀሃፊ ጋር ተወያዩ

By Mikias Ayele

June 28, 2024

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) ከኬንያ መንገድ እና ትራንስፖርት ካቢኔ ፀሃፊ ኪፕቹምባ ሞርኮሜን ጋር በኬንያ ተወያተዋል፡፡

በውይይታቸውም ሁለቱን ሀገራት በመሰረተ ልማት ማስተሳሰር በሚቻልባቸው ጉዳዮች መክረዋል።

በተጨማሪም የንግድ፣ የኢኮኖሚ ዕድገት እና የጋራ ትብብርን ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ምክክር ማድረጋቸውን ከኬንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በውይይቱ በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ባጫ ደበሌ መሳተፋቸው ተገልጿል።