አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የሚገኙት የአፍሪካ የቀድሞ እግርኳስ ከዋክብት ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ጎበኙ፡፡
የቱሪዝም ሚኒስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ እና የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር አብረሀም በላይ (ዶ/ር) ስለግንባታ ሂደቱ እና ፕሮጀክቱ ለኢትዮጵያውያን ስላለው ትርጉም ገለፃ አድርገውላቸዋል::
የቀድሞዎቹ የናይጄሪያ ኮከብ ተጫዋቾች ኑዋንኮ ካኑና ዳንኤል አሞካቺ፣ ሴኔጋላዊው ሄንሪ ካማራን ጨምሮ የኪነጥበብ ባለሙያዎችና የፉሽን ዲዛይነሮች በጉብኝቱ ከተሳተፉት መካከል መሆናቸውን የቱሪዝም ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡