የሀገር ውስጥ ዜና

በአዋሽ ተፋሰስ ቅድመ ጎርፍ መካለከል ሥራ ተጀመረ

By ዮሐንስ ደርበው

July 01, 2024

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ውኃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር በአዋሽ ተፋሰስ አካባቢ ሊደርስ የሚችለውን የጎርፍ አደጋ ቀድሞ መከላከል የሚያስችል ሥራ መጀመሩን አስታወቀ፡፡

ከዓለም ባንክ በተገኘ ድጋፍ ከፍተኛ የጎርፍ ሥጋት ባለበት የአዋሽ ተፋሰስ አካባቢ ዛሬ የተጀመረው የቅድመ ጎርፍ መከላከል ሥራ በሁለት ወራት እንደሚጠናቀቅ የውኃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ዴዔታ ሱልጣን ወሊ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

በላይኛው አዋሽ ባሉ ሰባት ወረዳዎች የተጀመረው የቅድመ ጎርፍ መከላከል ሥራ ሲጠናቀቅ ከ 27 ሺህ በላይ ቤተሠቦችን ከጎርፍ ሥጋት እንደሚከላከል እና ከ 10 ሺህ ሄክታር በላይ የእርሻ መሬትም ከጉዳት ይድናል ብለዋል፡፡

በቀጣይም የቅድመ ጎርፍ መከላከል ሥራው በሌሎች የተፋሠሡ አካባቢዎች እንደሚቀጥል አመላክተዋል፡፡

እንደ ሐገር የጎርፍ መከላከል ሥራ በሰባት ተፋሠሦች ላይ እየተሠራ ይገኛል

በሰሎሞን ይታየው