የሀገር ውስጥ ዜና

በአዲስ አበባ የሸማ ጥበብ ማዕከል ግንባታ ተጀመረ

By Meseret Demissu

June 18, 2020

አዲስ አበባ ፣ሰኔ 11 ፣2012 (ኤፍ፣ቢ.ሲ)የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በሽሮ ሜዳ የሸማ ጥበብ ማዕከል ግንባታ መጀመሩን ገለጹ።

ምክትል ከንቲባው በፌስ ቡክ ገጻቸውላ እንዳሰፈሩት÷”የአገራችን ጠቢባን እጅ ስራ ግሩም ድንቅ ሆኖ ፈትል ሸምኖ ሲያሞቀን ሲያደምቀን ኖሯል”ብለዋል።

”ጠቢባኑን ግን በሚመቻቸው መንገድ እንዲሰሩ፣ ስራቸው ተስፋፍቶ ሸማቸው አገር ከማልበስ ተሻግሮ ለአገር ኢኮኖሚ አስተዋፅኦ እንዲያደርግ አልተደረገም”ሲሉ ገልጸዋል።

ስለሆነም በከተማችን ብዙ የሸማ ጥበብ ስራ በሚሰራበት ሽሮ ሜዳ ማዕከል ሆኖ የሚያገለግል ግንባታ ጀምረናልም  ነው ያሉት።

ኢንጂነር ታከለ አያዘውም ”ከጥበቡ “ሸማ”ን ከሰፈሩ “ሜዳ”ን ወስደን የወደፊቱን የኢትዮጲያ ጥበብ ማበልፀጊያ ማዕከል “ሸማ ሜዳ”ን በፍጥነት አጠናቀን ለአገልግሎት እናበቃለን” ብለዋል።