አዲስ አበባ፣ ሰኔ 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ደስታ ሌዳሞ የዘንድሮውን ክልል አቀፍ የአረንጓዴ ዐሻራ የችግኝ ተከላ መርሐ- ግብር በሐዋሳ ዙሪያ ወረዳ ኡምቡሌ ዋጮ ቀበሌ በይፋ አስጀመሩ።
የዘንድሮው የአረንጓዴ ዐሻራ ችግኝ ተከላ መርሐ-ግብር የሚከናወነው “የምትተክል ሀገር የሚያጸና ትውልድ” በሚል መሪ ሐሳብ ነው፡፡
በክልሉ በዘንድሮ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር ለምግብነትና ለእንስሳት መኖነት የሚያገለግሉ ተክሎችን ጨምሮ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች እንደሚተከሉ መገለጹን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
የችግኝ ተከላው ከ29 ሺህ ሄክታር በሚልቅ መሬት ላይ እንደሚካሄድም ነው የተመላከተው፡፡