የሀገር ውስጥ ዜና

አፈ ጉባዔ ታገሠ ጫፎ የሥራ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁትን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር አሰናበቱ

By Melaku Gedif

July 05, 2024

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ታገሠ ጫፎ የሥራ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁትን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) አሰናበቱ።

ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ሆነው ሰኔ 25 ቀን 2011 ዓ.ም መሾማቸው ይታወሳል፡፡

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ታገሠ ጫፎ የአገልግሎት ጊዜያቸውን ያጠናቀቁትን ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) ማሰናበታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡