አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ከሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ምክትል ሰብሳቢ ሌተናል ጀኔራል መሐመድ ሃምዳን ደጋሎን ጋር በመሆን በአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ ጉብኝት አካሄዱ።
የሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ምክትል ሰብሳቢ ሌተናል ጀኔራል መሐመድ ሃምዳን ደጋሎ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ለመምከር በትናንትናው እለት አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወሳል።
ሌተናል ጀኔራል መሐመድ ሃምዳን ዳልጎ በትናንትናው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ጋር መገናኘታቸውም አይዘነጋም።
በዛሬው እለትም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ እና ሌተናል ጀኔራል መሐመድ ሃምዳን ደጋሎን በአዳማ ኢንዱስትሪያል ፓርክ ጉብኝት በማድረግ ላይ ይገኛሉ።
በጉብኝቱ ላይም የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናት ተሳፍተዋል።
ጉብኝቱን አስመልክቶም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በፌስቡክ ገፃቸው “ከሌተናል ጀነራል መሐመድ ሐምዳን ዳግሎ ጋር በመሆን፣ የአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክን ጎብኝተናል” ብለዋል።
“በዚህ የኮቪድ19 ወረርሽኝ ወቅት፣ ኢንዱስትሪዎቻችን መደበኛ ሥራቸውን በጊዜያዊነት ቀይረው ለሁኔታው አስፈላጊ የሆኑ ምርቶችን በማምረት ለመቋቋም መቻላቸውን ተመልክተናል” ሲሉም ገልፀዋል።
ከጉብኝቱ በኋላም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ እና ሌተናል ጀኔራል መሐመድ ሃምዳን ደጋሎ በኢንዱስትሪ ፓርኩ ቅጥር ግቢ ውስጥ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሂደዋል።
በአላዛር ታደለ
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።