የሀገር ውስጥ ዜና

የእርሻ ዕቅዳችንን ሊያሳካ የሚችል ሰፊ እንቅስቃሴ ተጀምሯል – ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

By Feven Bishaw

July 08, 2024

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የእርሻ ዕቅዳችንን ሊያሳካ የሚችል ሰፊ እንቅስቃሴ ተጀምሯል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለፁ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው÷ “ኩታ ገጠም እርሻ እየተስፋፋ ነው፤ የዚህ ክረምት የእርሻ ዕቅዳችንን ሊያሳካ የሚችል ሰፊ እንቅስቃሴ ተጀምሯል” ብለዋል።

እንቅስቃሴው መጠናከር አለበት ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በዚህ ዓመት ከ 24 ሚሊየን ሄክታር በላይ መሬት ለማረስ ዕቅድ መኖሩንም አስታውሰዋል።

ይህንን ዕቅድ ለማሳካትም ከዝናቡ ጋር መሽቀዳደም፣ ኩታ ገጠም ማድረግ፣ ዘመናዊ መንገድ መከተልም አለብን ነው ያሉት።

በምግብ ራስን ለመቻል የሚደረገውን ጥረት የሚያሳካው ይህ ጥረት መሆኑንም ጠቁመዋል።