የሀገር ውስጥ ዜና

በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች የተገነቡ የልማት ፕሮጀክቶች እየተመረቁ ነው

By Feven Bishaw

July 09, 2024

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች የተገነቡ የልማት ፕሮጀክቶች እየተመረቁ ነው፡፡

በሸገር ከተማ ገፈርሳ ጉጄ፣ ቡራዩና መልካ ኖኖ ክፍለ ከተሞች የተገነቡ የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶች በዛሬው ዕለት ተመርቀዋል።

በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባዔ ሰዓዳ አብዱራህማን፣ የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ተሾመ አዱኛ (ዶ/ር) እና ሌሎች የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

በተጨማሪም በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ኢሉ ወረዳ የተገነቡ የልማትፕሮጀክቶች ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደርገዋል፡፡

ፕሮጀክቶቹን የብልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ሃላፊ ፍቃዱ ተሰማ መርቀው ከፍተዋል፡፡

በተመሳሳይ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወሉ አብዲ በነቀምቴ ከተማ የተገነቡ የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶችን መርቀው መክፈታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡