የሀገር ውስጥ ዜና

ጠ/ሚ ዐቢይ(ዶ/ር) በቀድሞ የአሜሪካ ሴናተር ጂም ኢንሆፍ ህልፈት የተሰማቸውን ሃዘን ገለጹ

By Amele Demsew

July 09, 2024

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በቀድሞ የአሜሪካ ሴናተር ጂም ኢንሆፍ ህልፈት የተሰማቸውን ሃዘን ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ፥ የቀድሞ ሴናተር ጂም ኢንሆፍ የመርህ ሰው እና እውነተኛ የኢትዮጵያ ወዳጅ እንደነበሩ አንስተዋል፡፡

የሴናተሩን ህልፈት በመስማቴም አዝኛለሁ ያሉ ሲሆን ፤ ሁሌም የሚታወሱ ሰው መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡