የሀገር ውስጥ ዜና

አፈ ጉባዔ ታገሠ ጫፎ በቀድሞ የአሜሪካ ሴናተር ጂም ኢንሆፍ ሕልፈት የተሰማቸውን ሃዘን ገለጹ

By Melaku Gedif

July 10, 2024

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አፈ ጉባዔ ታገሠ ጫፎ በቀድሞ የአሜሪካ ሴናተር ጂም ኢንሆፍ ሕልፈት የተሰማቸውን ሃዘን ገልጸዋል፡፡

አፈ ጉባዔው በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ሴናተር ጂም ኢንሆፍ በደስታም ሆነ በችግር ጊዜ እውነተኛ የኢትዮጵያ ወዳጅ እንደነበሩ አውስተዋል፡፡