የሀገር ውስጥ ዜና

“ለ #ጽዱኢትዮጵያ ንቅናቄ ጥሪ ስናቀርብ ዜጎቻችን በከፍተኛ ተነሳሽነት በሥራው ተሳትፈዋል-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

By Feven Bishaw

July 11, 2024

 

ዋናው አላማችን አካባቢያችንን ሳቢ በማድረግ መፀዳጃ ቤት የመጠቀም ባህላችንን ከመሠረቱ ማዳበር ነበር።

ዛሬ በዜጎቻችን በዋጋ የማይተመን የልብ መዋጮ እና እምነት የተገነቡትን ሥራዎች በቦታው በመገኘት ገምግመናል።

ከፍተኛ ጥራት ባላቸው ጠንካራ እና ዘመን ተሻጋሪ በሆኑ ቁሶች በመጠቀም ደረጃቸውን የጠበቁ የህዝብ መፀዳጃ ቤቶች ለመገንባት ቁርጠኝነት ይዘናል።

ይህ የሥራው መጀመሪያ ነው። በእናንተ ያላሰለሰ ድጋፍ የጀመርናቸውን ሥራዎች እናስፋፋለን።” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)