ዓለምአቀፋዊ ዜና

አዲሱ የብሩንዲ ፕሬዚዳንት ቃለ መሀላ ፈጸሙ

By Meseret Demissu

June 18, 2020

አዲስ አበባ ፣ሰኔ 11 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የቡሩንዲ አዲስ ፕሬዚዳንት ሆነው የተመረጡት የ52 ዓመቱ  ኢቫሪስቴ ናዴሽሚሚዬ  ዛሬ ቃለ መሀላ ፈጸሙ።

ንዴይሺሚዬ  በብሩንዲ  ባለፈው ግንቦት ወር በተካሄደው  ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ አሸናፊ መሆናቸው ተገልጾ ነበር።

ፕሬዚዳንቱ ቃለ መሃላ ይፈጽማሉ ተብሎ የተጠበቀው በመጪው ነሀሴ ወር ነበር።

ሆኖም  የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት  የነበሩት ኑኩሩንዚዛ  ባለፈው ሳምንት በልብ ህመም  በድንገት ህይወታቸው ማለፉን ተከትሎ÷ አዲሱ ፕሬዚዳንት ቃለ መሃላቸውን ይፈጽማሉ ተብሎ ከተጠበቀው  ሁለት ወራት ቀደም ብለው ዛሬ ፈጽመዋል።

አዲሱ ፕሬዚዳንቱ የአገሪቱ አስተዳደር ዋና ከተማ በሆነችው ጌቲጋ  ቃለ መሃላቸውን ሲፈጽሙ  የውጭ ሀገራት መሪዎች አለመገኘታቸው ተነግሯል።

የቀድሞው ፕሬዚዳንት  15 ዓመታት በስልጣን ላይ የቆዩ ሲሆን በመጪው  በነሐሴ ወር  ለአዲሱ ፕሬዚዳንት ስልጣናቸውን ለመልቀቅ በዝግጅት ላይ ነበሩ ተብሏል

ሆኖም በፈረንጆቹ ሰኔ 8  በ 55 ዓመታቸው  በልብ ህመም ሕይወታቸው ማለፉን መንግስት አስታውቆ ነበር።

አንዳንድ ያልተረጋገጡ ዘገባዎችም የፕሬዚዳንቱ ሞት ከኮቪድ -19 ጋር የተያያዘ መሆኑን  አንስተዋል።

ሚስተር ንዴይሺሚዬ እንደ  ቀድሞው መሪ  ንኩሪዚዛ  ሁሉ የአማጽን መሪ እንደነበሩ ይነገርላቸዋል  ፡፡

ምንጭ፡- ቢ.ቢ.ሲ

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።