የሀገር ውስጥ ዜና

ርዕሰ መሥተዳድር ሽመልስ አብዲሳ በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን በኩታ ገጠም እየለማ የሚገኝ የስንዴ ሰብልን ጎበኙ

By ዮሐንስ ደርበው

July 15, 2024

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ የፌደራል እና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን በኩታ ገጠም እየለማ የሚገኝን የስንዴ ሰብል ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝታቸውም በዞኑ ቀርሳ ማሊማ ወረዳ እየለማ ያለውን የስንዴ ሰብል መጎብኘታቸው ተገልጿል፡፡

በተመሳሳይ አቶ ሽመልስን ጨምሮ የፌዴራልና የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በምስራቅ ሸዋ ዞን እና አዳማ ከተማ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ፕሮጀክቶችን በትናንትናው ዕለት መጎብኘታቸው ይታወሳል፡፡

በትናንቱ ጉብኝታቸውም በምሥራቅ ሸዋ ዞን እና በአዳማ ከተማ አስተዳደር የነዋሪዎችን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥና ስራ አጥነትን ለመቀነስ በመገንባት ላይ ያሉ የልማት ፕሮጀክቶች ተመልክተዋል፡፡