የሀገር ውስጥ ዜና

አቶ ሽመልስ አብዲሳ በምዕራብ ሸዋ ዞን የልማት ሥራዎችን ጎበኙ

By ዮሐንስ ደርበው

July 16, 2024

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ አመራሮች በምዕራብ ሸዋ ዞን እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝታቸውም በአምቦ ከተማ በመከናወን ላይ የሚገኙ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መመልከታቸው ተገልጿል፡፡

ርዕሰ መሥተዳድሩን ጨምሮ የፌደራል እና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በትናንትናው ዕለት በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን የልማት ሥራዎችን መጎብኘታቸው ይታወሳል፡፡