የሀገር ውስጥ ዜና

በትራፊክ አደጋ የ6 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ 14 ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት ደረሰ

By ዮሐንስ ደርበው

July 16, 2024

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሌ ክልል ቀብሪበያህ ወረዳ ጉዮው በተባለ ቦታ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሥድስት ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡

በተጨማሪም በ14 ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት መድረሱ ተገልጿል፡፡

አደጋው የተከሰተው በሁለት መኪኖች ግጭት መሆኑም ነው የተመላከተው፡፡