የሀገር ውስጥ ዜና

በጌዴኦ ዞን በተከሰተ የትራፊክ አደጋ የሟቾች ቁጥር 9 ደረሰ

By ዮሐንስ ደርበው

July 17, 2024

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጌዴኦ ዞን ጮርሶ ወረዳ ዲባንድቤ ቀበሌ ሻይሳ አካባቢ ዛሬ ረፋድ 5 ሠዓት ላይ በተከሰተ የትራፊክ አደጋ የዘጠኝ ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ በአራት ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ደረሰ፡፡

አደጋው የተከሰተው “ሲኖ ትራክ” እየተባለ የሚጠራው የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪ ከዲላ ወደ ሞያሌ ከሚጓዝ “ዶልፊን” የሕዝብ ማመላለሻ እና ከቡሌ ሆራ ወደ ዲላ ሲጓዝ ከነበር “ኤፍ ኤስ አር” ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ ነው ተብሏል፡፡