የሀገር ውስጥ ዜና

በታች አርማጭሆ ወረዳ 7 ሺህ 500 የክላሸ ጥይት ተያዘ

By Mikias Ayele

July 17, 2024

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰሜን ምዕራብ ዕዝ አንድ ክፍለጦር በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ታች አርማጭሆ ወረዳ 7 ሺህ 500 የክላሸ ጥይት መያዙን አስታወቀ፡፡

የክፍለጦሩ አዛዥ ኮሎኔል ግርማ መሃመድ÷ ህገ ወጥ ጥይቱ ከሳንጃ ከተማ ሰጋሎ ወደ ተባለ አካባቢ ሲጓጓዝ መያዙን ገልጸው፤ በህገ-ወጥ ድርጊቱ ላይ ተሳታፊዎችን  በቁጥጥር ስር ለማዋል ተጨማሪ ምርመራ እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።

በተጨማሪም በወረዳው የመንግስትን የሠላም አማራጭ የተቀበሉ 9 ታጣቂዎች ከነ ሙሉ ትጥቃቸው እጅ መስጠታቸውን አዛዡ ገልፀዋል፡፡

በአካባቢው ሰላም ለማስፈን በሚያደርገው ጥረት የአካባቢው ማህበረሰብ መረጃ በመስጠት እያደረገ ያለውን ትብብር አጠናክሮ እንዲቀጥልም መጠየቃቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡