የሀገር ውስጥ ዜና

በሸበሌ ወንዝ ዙሪያ እየተሰሩ ያሉ የልማት ስራዎች የጎዴን ዕድገት እያፋጠኑ ነው- ም/ጠ/ሚ ተመስገን ጥሩነህ

By ዮሐንስ ደርበው

July 17, 2024

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሸበሌ ወንዝ ዙሪያ እየተሰሩ ያሉ የልማት ስራዎች የጎዴን ዕድገት እያፋጠኑ ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ፡፡

የዋቢ ሸበሌ ወንዝ ውሃን በማጣራት ለመጠጥ ብቁ የሚያደርገውን የጎዴ ከተማ ፕሮጀክት መጎብኘታቸውን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡

በዚህም በሸበሌ ወንዝ ዙሪያ እየተሰሩ ያሉ የልማት ስራዎች የጎዴ ከተማን ዕድገት እያፋጠኑት ነው ብለዋል፡፡