የሀገር ውስጥ ዜና

በ1 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር የተገነባው የደራርቱ ቱሉ የስፖርት ማሰልጠኛና ምርምር ኢንስቲትዩት ተመረቀ

By Feven Bishaw

July 18, 2024

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሸገር ከተማ አስተዳደር ሱሉልታ ከተማ በ1 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ወጪ የተገነባው የደራርቱ ቱሉ የስፖርት ማሰልጠኛና ምርምር ኢንስቲትዩት ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል፡፡

በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ሰአዳ አብዱራህማን፣ የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ እና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

ኢንስቲትዩቱ የተለያዩ አገልግሎቶች የሚሰጡ ከ40 በላይ ህንፃዎች ያሉት ሲሆን÷ በአንድ ጊዜ ከ800 በላይ አሰልጣኞችን ማሰልጠን ይችላል ነው የተባለው።

በደጀኑ ጎንፋ