የሀገር ውስጥ ዜና

ጨፌ ኦሮሚያ 7ኛ መደበኛ ጉባዔውን ማካሄድ ጀመረ

By Shambel Mihret

July 21, 2024

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ እና ነገ የሚደረገው የጨፌ ኦሮሚያ 6ኛ የስራ ዘመን 3ኛ ዓመት 7ኛ መደበኛ ጉባዔ ዛሬ በአዳማ ከተማ ገልማ አባገዳ አዳራሽ መካሄድ ጀምሯል።

በጉባዔው የተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ውይይት ተደርጎ ውሳኔዎች ይተላለፍባቸዋል ተብሎ ይጠበቃል።

የክልሉ የ2016 በጀት ዓመት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት የሚደረግበት ሲሆን፤ የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ጨፌው ይመክራል ተብሎ ይጠበቃል።

እንዲሁም የክልሉ መንግሥት በጀት ለጉባኤው ቀርቦ ውይይት ከተደረገበት በኋላ ይፀድቃል ተብሏል።

በመራኦል ከድር