የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮ ቴሌኮም በጎፋ ዞን በደረሰዉ የመሬት መንሸራተት አደጋ ለተጎዱ ድጋፍ ማሰባሰቢያ አጭር የመልዕክት ቁጥር ይፋ አደረገ

By ዮሐንስ ደርበው

July 24, 2024

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮ ቴሌኮም በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን አደጋ መከላከልና ዝግጁነት ጋር በመተባበር በጎፋ ዞን በደረሰዉ ድንገተኛ የመሬት ናዳ ምክንያት ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ ማሰባሰቢያ አጭር የመልዕክት ቁጥር ይፋ አደረገ።

ኩባንያው ዜጎች ወደ 8091 ወይም በቴሌብር ሱፕርአፕ የፈለጉትን የብር መጠን በመላክ ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች መደገፍ እንደሚችሉ አስታውቋል።

ኢትዮ ቴሌኮም በዞኑ ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው አሳዛኝ ክስተት ምክንያት የወገኖቻችን ሕይወት በማለፉ የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን በመግለጽ ጉዳት ለደረሰባቸው ቤተሰቦች፣ ለክልሉ ህዝቦች እና ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ መጽናናትን ተመኝቷል።