የሀገር ውስጥ ዜና

ሆስፒታሉ ነጻ የጤና ምርመራ አገልግሎት አስጀመረ

By ዮሐንስ ደርበው

July 26, 2024

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ ለ50 ሺህ ሰዎች ነጻ የጤና ምርመራ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችለውን መርሐ-ግብር ማስጀመሩን አስታወቀ፡፡

መርሐ-ግብሩ የሚካሄደው “በጎነት ለጤናችን” በሚል መሪ ሐሳብ መሆኑንም ገልጿል፡፡

የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ መርሐ-ግብሩን ባስጀመሩበት ወቅት ባደረጉት ንግግር÷ ማንኛውም ሰው በምርመራ ማዕከሉ በመገኘት የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆን እንደሚችል አስታውቀዋል፡፡