የሀገር ውስጥ ዜና

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ አመራሮች ከደቡብ ሱዳን ሪፐብሊክ የመከላከያ አመራሮች ጋር ተወያዩ

By Feven Bishaw

July 28, 2024

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ አመራሮች ከደቡብ ሱዳን ሪፐብሊክ የመከላከያ አመራሮች ጋር ተወያይተዋል።

ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮቹ በሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች እንዲሁም የጋራ ደህንነትን ማስጠበቅ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት የፌስቡክ ገፅ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።