የሀገር ውስጥ ዜና

በይርጋጨፌ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ3 ሰዎች ሕይወት አለፈ

By Shambel Mihret

July 28, 2024

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጌዴኦ ዞን ይርጋጨፌ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሶስት ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡

አደጋው መነሻውን ሞያሌ ያደረገና የአፈር ማዳበሪያ የጫነ ከባድ ተሽከርካሪ ከሞተር ሳይክል ጋር በመጋጨቱ ነው የተከሰተው፡፡

የትራፊክ አደጋው በይርጋጨፌ ወረዳ ወቴ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ዛሬ ከጠዋቱ 4 ሰዓት አካባቢ መከሰቱን የዞኑ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል።