ዓለምአቀፋዊ ዜና

በብራዚል በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ1 ሚሊየን አልፏል

By Tibebu Kebede

June 20, 2020

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 13 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በብራዚል በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ1 ሚሊየን አልፏል።

ሃገሪቱ ከ1 ሚሊየን በላይ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎችን ቁጥር በማስመዝገብ ዓለም ላይ ሁለተኛዋ ሃገር ሆናለች።

የሃገሪቱ ጤና ሚኒስቴር እንዳስታወቀው አሁን ላይ በሃገሪቱ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 1 ሚሊየን 38 ሺህ ደርሷል።

ባለፉት 24 ሰአታት ብቻም ከ54 ሺህ በላይ ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል ነው ያለው።

ከዚህ በተጨማሪም ከ1 ሺህ 200 በላይ ሰዎች ለህልፈት ተዳርገዋል ነው የተባለው ይህም በአጠቃላይ በቫይረሱ ሳቢያ ለህልፈት የተዳረጉ ዜጎችን 49 ሺህ አድርሶታል።

በሃገሪቱ ያለው የመመርመር አቅም ውስንነት አሁንም እንደችግር ይነሳል።

በሌሌ በኩል የዓለም ጤና ድርጅት ኮሮና ቫይረስ አዲስ እና አደገኛ ደረጃ ላይ ደርሷል ሲል አስጠንቅቋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ