የሀገር ውስጥ ዜና

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራሙን በብቃት እና በውጤታማነት ለመተግበር መንግሥት ያስቀመጣቸው ቁልፍ ስትራቴጂካዊ አቅጣጫዎች፡-

By Melaku Gedif

July 28, 2024

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራሙን በብቃት እና በውጤታማነት ለመተግበር መንግሥት ያስቀመጣቸው ቁልፍ ስትራቴጂካዊ አቅጣጫዎች፡-

👉 ዋና ዋና የፖሊሲ ርምጃዎች ከአጠቃላይ ሀገራዊ የረጅምና የመካከለኛ ዘመን የልማት ዕቅዶቻችን ጋር ተጣጥመው ይከናወናሉ፣

👉 የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም በሚያስጠብቅና የዜጎችን ተጠቃሚነት በሚያረጋግጥ መልኩ እንዲተገበሩ ከፍተኛ የክትትልና የድጋፍ ማዕቀፎችን ይዘረጋል፣

👉 በሚመለከታቸው ተቋማት በኩል የፖሊሲ ትግበራ አፈጻጸም ወጥነት እንዲኖር መንግሥት ጠንካራ የፖሊሲ ማሻሻያ አመራር መኖሩን ያረጋግጣል፣

👉 መንግሥት እንደ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ፣ የገንዘብ ሚኒስቴር እና የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ላሉ ቁልፍ የማክሮ ኢኮኖሚ ተቋማት ድጋፍ በማድረግ ተቋማዊ ዐቅምን ያጠናክራል፣

👉 ተቋማቱ የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲዎችን በማውጣት፣ በመተግበር እንዲሁም ተጽዕኗቸውን በመከታተልና በመገምገም ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ፣

👉 መንግሥት ለማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራሙ ድጋፍን ለማሰባሰብ ከሁሉም ባለ ድርሻ አካላት ጋር ግልጽነት ያለው ግንኙነት ይፈጥራል፣

👉 ተጋላጭ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ለመደገፍ የሚያስችሉ ተግባራት ይከናወናሉ፤ የማኅበራዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራሞች ድጎማ ይደረግላቸዋል፤ ለዝቅተኛ ደመወዝ ተከፋይ የመንግሥት ሠራተኞች የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዎቹ ሊያስከትሉ ከሚችሉት የአጭር ጊዜ አሉታዊ ተጽዕኖዎች ለመጠበቅ አስፈላጊ የደሞዝ ድጎማና ማሻሻያዎች ለተወሰኑ ጊዜያት ይደረጋሉ፣

👉 የነዳጅ ዋጋ ጭማሪውን መንግስት በከፊል የሚደጉም ይሆናል፤ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ሂደት ቀጣይነት ያለው ግምገማ ይደረግለታል፣

👉 መንግሥት በወቅታዊ መረጃ ላይ በመመሥረት በፕሮግራሙ ላይ ወቅታዊ፣ አስፈላጊ እና ተገማች የፖሊሲ ማስተካከያዎችን ያደርጋል፣

👉 የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ሂደት ተከትሎ በኢኮኖሚው ውስጥ ሊከሠት የሚችለውን የመልካም አስተዳደር ብልሹነት እና ሕገ ወጥነት ለመከላከል መንግሥት የነቃ ቁጥጥር በማድረግ ርምጃ ይወስዳል።