የሀገር ውስጥ ዜና

ጠ/ሚ ዐቢይ ለአዲሱ የቡሩንዲ ፕሬዚዳንት የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ

By Tibebu Kebede

June 20, 2020

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 13 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለአዲሱ የቡሩንዲ ፕሬዚዳንት ኢቫሪስቴ ንዳይሺሚዬ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስ ቡክ ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ከፕሬዚዳንቱ ጋር የጋራ በሆኑ አካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ እንደሚሰሩ እምነታቸው መሆኑንም ገልጸዋል።

ፕሬዚዳንት ኢቫሪስቴ ንዳይሺሚዬ ከትናንት በስቲያ ቃለ መሃላ መፈጸማቸው ይታወሳል።

ፕሬዚዳንቱ ባለፈው ግንቦት ወር በተካሄደ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ማሸነፋቸው መገለጹ የሚታወስ ነው።

ፕሬዚዳንቱ ቃለ መሃላ ይፈጽማሉ ተብሎ የተጠበቀው በመጭው ነሐሴ ወር ነበር።

የቀድሞው የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ኑኩሩንዚዛ ባለፈው ሳምንት በልብ ህመም በድንገት ህይወታቸው ማለፉን ተከትሎ÷ አዲሱ ፕሬዚዳንት ቃለ መሃላቸውን ይፈጽማሉ ተብሎ ከተጠበቀው ሁለት ወራት ቀደም ብለው ፈጽመዋል።