የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያ በቻይና-አፍሪካ ዲጂታል ትብብር መድረክ እየተሳተፈች ነው

By ዮሐንስ ደርበው

July 29, 2024

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በቤጂንግ እየተካሄደ በሚገኘው በቻይና-አፍሪካ ዲጂታል ትብብር መድረክ ላይ እየተሳተፈች ነው፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) በመድረኩ ላይ ንግግር አድርገዋል፡፡

በንግግራቸውም በዲጂታል ፈጠራ ዘርፍ በኢትዮጵያ እና ቻይና መካከል ለውጥ የሚያመጣ ጠንካራ ትብብር መኖሩን በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡