አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለመጪው ረቡዕ ሐምሌ 24 ቀን 2016 ዓ.ም አስቸኳይ ስብሰባ ጠርቷል፡፡
በኢፌዴሪ ሕገ-መንግሥት አንቀፅ 58 ( 4) እና በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአሰራርና የአባላት ሥነ- ምግባር ደንብ ቁጥር 6/2008 አንቀፅ 15 ( 1 ና 2) መሰረት ምክር ቤቱ በዕረፍት ላይ እያለ የምክር ቤቱን ውሳኔ የሚሹ አስቸኳይ ጉዳዮች ሲያጋጥሙ የምክር ቤቱ አፈ-ጉባኤ አስቸኳይ ስብሰባ ሊጠራ እንደሚችል ተደንግጓል፡፡
በዚህ መሰረትም ለረቡዕ ሐምሌ 24 ቀን 2016 ዓ.ም የምክር ቤቱ አፈ-ጉባኤ አስቸኳይ ስብሰባ ጠርተዋል፡፡
ስለሆነም የ6ኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በዕለቱ ከቀኑ 7፡30 ጀምሮ ሪፖርት በማድረግ በአስቸኳይ ስብሰባው እንዲገኙ ምክር ቤቱ ጥሪ አቅርቧል፡፡