የሀገር ውስጥ ዜና

በሕገ-ወጥ መንገድ ሲጓጓዝ የነበረ 121 በርሜል ቤንዚን ተያዘ

By Mikias Ayele

July 31, 2024

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሕገ-ወጥ መንገድ በተሽከርካሪ ሲጓጓዝ የነበረ 121 በርሜል ቤንዚን መያዙን የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን አስታወቀ፡፡

ቤንዚኑ የተያዘው ለፌዴራል ፖሊስ የተሰጠውን ጥቆማ ተከትሎ በተደረገ ክትትል በአዲስ አበባ ዙሪያ ቡራዩ ኬላ ፀረ-ኮንትሮባንድ መቆጣጠርና መከላከል መምሪያ ሬጅመንት አማካኝት መያዙን የባለስልጣኑ መረጃ አመላክቷል፡፡

ተሽከርካሪው መነሻውን ኦሮሚያ ክልል ቢሾፍቱ ከተማ መዳረሻውን ደግሞ ምዕራብ ወለጋ ቤጊ ወረዳ በማድረግ ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ ለአደጋና ብክነት በተጋለጠ ሁኔታ ቤንዚን ጭኖ ሲንቀሳቀስ ነበር ተብሏል፡፡