የሀገር ውስጥ ዜና

የአማራ ክልል የ2017 በጀት ከ150 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በላይ ሆኖ ጸደቀ

By ዮሐንስ ደርበው

July 31, 2024

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል መንግሥት የ2017 በጀት ከ150 ቢሊየን 666 ሚሊየን ብር በላይ ሆኖ ጸድቋል፡፡

የአማራ ብሔራዊ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር፣ 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 8ኛ መደበኛ ጉባዔ በዛሬው ውሎው የክልሉን መንግሥት የ2017 በጀት ተወያይቶ አጽድቋል፡፡

በዚህም የክልሉን መንግሥት የ2017 በጀት 150 ቢሊየን 666 ሚሊየን 531 ሺህ 527 ብር አድርጎ ማጽደቁን አሚኮ ዘግቧል፡፡