አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት በይበልጥ አጠናክራ እንደምትቀጥል በኢትዮጵያ የሀገሪቱ አምባሳደር ዣኦ ዢዩዋን አረጋገጡ፡፡
የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮችን ጨምሮ የኢትዮጵያ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት የቻይና ሕዝባዊ ጦር 97ኛ ዓመት የምስረታ በዓል በአዲስ አበባ ተከብሯል፡፡
በዚሁ ወቅት አምባሳደር ዣኦ ዢዩዋን ባደረጉት ንግግር÷ ቻይና ለኢትዮጵያ ልማት፣ ሰላም እና ብልጽግና እንደምትሠራ አስረድተዋል፡፡
ዕድሎችን ለመጠቀም ብሎም ፈተናዎችን ለመሻገር ከኢትዮጵያና ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ጋር በትብብር እንሠራለን ሲሉም አረጋግጠዋል፡፡
በመጪው መስከረም ወር የሚካሄደው የቻይና-አፍሪካ ጉባዔም ለዚህ መሠረት የሚጥል መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡
በአፈወርቅ እያዩ