የሀገር ውስጥ ዜና

ለጎፋ ዞን 4 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር ድጋፍ ተደረገ

By Feven Bishaw

August 02, 2024

 

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በጎፋ ዞን በመሬት መንሸራተት ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የሚውል 4 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር ዋጋ ያለው የዓይትና የጥሬ ገንዘብ ድጋፍ አደረገ፡፡

የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) በአደጋው በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ሐዘን ገልጸው÷ 2 ሚሊየን ብር በጥሬ ገንዘብ እና 2 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር ዋጋ ያለው የዓይነት ድጋፍ ማድረጋቸውን አስታውቀዋል፡፡

ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ መግለጻቸውን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡

በተመሳሳይ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በመሬት መንሸራተት ጉዳት ለደረሰባቸው የሚውል አምስት ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል።

የአገልግሎቱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሽፈራው ተሊላ ድጋፉን ባስረከቡበት ወቅት ÷ በመልሶ ማቋቋም ሥራውም አስፈላጊውን ድጋፍ እናደርጋለን ብለዋል፡፡